ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አልጠይቅም ብላለች
በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረውና ክስ ተመስርቶባቸው
ከዕድሜ ልክ እስከ አስራ አራት ዓመት እስር የተፈረደባቸው እነ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መንግሥትን ይቅርታ ጠየቁ፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል
አንዷ የሆነችውና አስራ አራት አመት እስር የተፈረደባት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ይቅርታ እንደማትጠይቅ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት
ታዬ፣ ሒሩት ክፍሌ እና አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ለፍትህ ሚ/ር ባስገቡት ማመልከቻ መንግስትን በይቅርታ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን
ሦስቱም ፍርደኞች የጀመሩትንም የይግባኝ ጥያቄ እንዳቋረጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከእነጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ጋር ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶባት
የአስራ አራት ዓመት እስርና የ33ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባት መምህርትና ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ፤ ይቅርታ እንደማትጠይቅ
ገልፃለች፡፡ እነ ውብሸት ታዬ ለፍትህ ሚኒስቴር ያስገቡትን ማመልከቻ
መልስ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የገለፁት ምንጮች፤ ምላሹ ፈጣን ይሆናል ብለው በማሰባቸው የይግባኙን ሒደት እንዳጀቋረጡት ተናግረዋል፡፡
ፍ/ቤት ጥፋተኝነታቸውን አረጋግጦ በሰጠው የፍርድ
ብያኔ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ የ14 ዓመት እስርና የ33ሺህ ብር ቅጣት፣ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር የ17 ዓመት እስርና የ50ሺህ
ብር ቅጣት እንዲሁም ሂሩት ክፍሌ የ19 ዓመት እስርና የ50ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡
No comments:
Post a Comment