በመጪው
ቅዳሜ የሚለቀቀው የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) “ጥቁር ሰው” አልበም ማስተዋወቂያ የሆነው ‘ኦ አፍሪካ’ የተባለው የሞባይል ጥሪ ድምፅ (Ringtone) 100 ሺሕ ኮፒ ለተጠቃሚዎች ተሸጠ፡፡
Michael Hailu: The talent behind Teddy Afro |
‘ኦ
አፍሪካ’ የሚለው ዘፈን በአቡጊዳ ባንድ መቀናበሩ ታውቋል፡፡ በሞባይል ስልኩ ጥሪውን ለመጫን የሚፈልግ ማንም ሰው በአጭር የስልክ መልዕክቱ ጥሪ ሲቀርብለት ከተስማማ ሁለት ብር ይቆረጥበታል፡፡ ይህ የስልክ መጥርያ ማስታወቂያ (Ringtone
Promotion) አዲስ
የሆነ የማስተዋወቂያ ዘዴ መሆኑን የገለጸው አዲካ፣ ሌሎች ዘፈኖቹን በዚህ መንገድ እንደሚያስተዋውቅ ገልጿል፡፡ የቴዲ አፍሮ ዘፈን በዚህ የማስተዋወቅ ዘዴ ለሚሊዮኖች ተልኮ በሺዎች የሚቆጠሩት ሲገዙት ይህ ለመጀመርያ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡
“በጥቀር
ሰው” አልበም ውስጥ አሥራ አንድ ዘፈኖች የተካተቱ ሲሆን፣ ዘጠኝ ዘፈኖችን ያቀናበረው ወጣቱ ሙዚቀኛ ሚካኤል ኃይሉ ነው፡፡ የአልበሙ መጠርያ የሆነውን “ጥቁር ሰው” ያቀናበረው ታዋቂው አቀናባሪ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺዎታ ነው፡፡
የአልበሙን
ሙሉ ግጥምና ዜማ የደረሰው ራሱ ቴዲ አፍሮ ሲሆን፣ ለየት ባለ ሁኔታም የታዋቂው ገጣሚና የቴአትር ጸሐፊ የሟቹ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅንም ድምፅ ተካቶበታል፡፡ “ኃይል” በሚለው ዘፈን ላይ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን “ፈራን” የሚል መጠርያ ያለውን ግጥሙን በማንበብ ተሳትፎበታል፡፡
አልበሙም
ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለአዲስ አበባና ለክልል አድማጮች በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤትና በአምባሰል ሙዚቃ ቤት አማካይነት የሚሰራጭ ሲሆን፣ ለሰሜን ኢትዮጵያ አድማጮች ደግሞ በጣና ኢንተርቴይመንት በኩል ይሰራጫል፡፡
ይህን
አልበም ፕሮዲዩስ ያደረገው፣ እያሰራጨና እያስተዋወቀ ያለው አዲካ ኮሙኒኬሽንና ኢቨንትስ ከቤሌማ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ሲሆን፣ ብቸኛ ስፖንሰሩም ሜታ ቢራ ነው፡፡
ቴዲ
አፍሮ “ጥቁር ሰው” ለተባለው አልበሙ 4.6 ሚሊዮን ብር እንደተከፈለው ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ቢገለጽም፣ አዲካ ግን የገንዘቡን መጠን ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ይህ ክፍያ በተለያዩ አካላት የተለያዩ መጠኖች ቢገለጽም፣ ትክክለኛውን ክፍያ ለማወቅ ፈጽሞ አልተቻለም፡፡
http://www.ethiopianreporter.com
http://www.ethiopianreporter.com
No comments:
Post a Comment