Thursday, April 5, 2012

ኢትዮጵያዊው ገጣሚ፣ ደራሲና ፀሃፌተውኔት ለምን ሲሳይ


ኢትዮጵያዊው ገጣሚ፣ ደራሲና ፀሃፌተውኔት ለምን ሲሳይ በመላው እንግሊዝ ከሚገኙ ዕውቅና ምርጥ ገጣሚዎች በቀዳሚነት ስሙ ይጠቀሳል፡፡ በዓለም አቀፍ ፀሃፊነቱ የሚታወቀው ለምን ሲሳይ፤ አምስት የግጥም መድበሎችን በእንግሊዝኛ ፅፎ አሳትሟል፡፡ የጥቁር እንግሊዛውያን ዘመነኛ ገጣሚዎችን ሥራዎች ያካተተውን “The Fire people” የግጥም መድበል የአርትኦት ስራም እንደሰራ ይናገራል፡፡ ለታዋቂው “Poetry Review” በመደበኛነት ፅሁፎችን የሚያቀርበው ገጣሚ ለምን፤ The Avron Poetry prize የተሰኘውን ውድድር ጨምሮ በሌሎች ትላልቅ የሥነ ፅሁፍ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ሰርቷል፡፡ ቢቢሲን ጨምሮ ለተለያዩ አካላት ኮሚሽን እየተደረገ በርካታ ግጥሞችን የፃፈው ገጣሚው፤ በማንችስተርና ሌሎች ከተሞች ህንፃዎችና ጐዳናዎች ላይ ግጥሞቹ እንደ መፈክርና ማስታወቂያ የተፃፉለት ገጣሚ ነው፡፡

ግጥሞቹ ተወዳጅ ከመሆናቸው የተነሳ መፅሃፍቱ በደንብ መሸጣቸውን የሚናገረው ለምን ሲሳይ፤ የግጥም አልበሙ በሚሊዮን ቅጂዎች እንደተቸበቸቡለት ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ገጣሚው ሦስት የመድረክ ቲያትሮችንም ፅፏል - Chaos by Design (1994) Storm (2003) እና something Dark (2006) የሚሏቸውን፡፡



በእንግሊዝ ላንክሻየር ግዛት የተወለደው ለምን፤ ከእናትና አባቱ ጋር ለማደግ አልታደለም፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 ወደ እንግሊዝ የመጡት እናቱ፤ በገጠማቸው አስቸጋሪ ሁኔታ በሰሜን እንግሊዝ ነዋሪ ለነበሩ ነጭ አሳዳጊዎች “ለአጭር ጊዜ” በሚል በአደራ ለመስጠት መገደዳቸውን ያስታውሳል፡፡ የዛሬ ስድስት ዓመት ለቢቢሲ ስለልጅነቱ የተናገረው ለምን ሲሳይ፤ ከእናቱ ጋር የተገናኘው ከረዥም ዓመት በኋላ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከሦስት ዓመት ፍለጋ በኋላ በ21 ዓመቴ ወላጅ እናቴን አገኘኋት ብሏል - ለምን፡፡ ከአሳዳጊዎቹ ጋር ለ11 ዓመት ከኖረ በኋላም ለልጆች አሳዳጊ ተቋም እንደተሰጠ ይናገራል፡፡ ለምን ሲሳይ ከነጭ አሳዳጊዎቹ ጋር ያሳለፈውን ጊዜ በበጐ አያስታውሰውም፡፡ “ምንም እንኳን ነጮች ቢሆኑም፣ ወላጅ አባትና እናቴ እንደሆኑ አምኜ ተቀብዬ ነበር” የሚለው ለምን፤ ዕድሜዬ 17 እስኪሆን ድረስ ከራሴ ሌላ ጥቁር አላውቅም ነበር ብሏል፡፡ የልጅነት ህይወቴን በሃሳብ ባቡር ወደ ኋላ ተንሻትቼ ሳስታውሰው፣ በማላውቀው የባዕድ ከባቢ እንዳደግሁ ይሰማኛል ይላል፡፡ይህንን መግቢያ የወሰድኩት ታዋቂው የእንግሊዝ ገጣሚ የ46 ዓመቱ ለምን ሲሳይ፤ ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎት ስለ ህይወቱና ስለ ሙያው ንግግር ካደረገ በኋላ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ጋር በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጥበብ አምድ ካደረገው ቃለ ምልልስ ነው፡፡ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ከፈለጋችሁ ከዚህ አንብቡ፡፡http://www.addisadmassnews.com ለእኔ ሲሳይ አዲስ ግን አስገራሚ ሰው ነው፡፡ቢቢሲ እ.ኤ.አ  በ1995 ለምን ሲሳይ ቤተሰቦቹን ፍለጋ የደረገውን ጉዞ ተከትሎ የሰራውን ዶክመንታሪ ፊልም እነሆ፡፡እንደ እኔ በሰውየው ለተማረካችሁ

ስለ ለምን ሲሳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የድረ ገፅ አድራሻውን ተጠቀሙ http://www.lemnsissay.com ወይም 


ክፍል 1

 

ክፍል 2



ክፍል 3

No comments:

Post a Comment