Friday, November 2, 2012

EBS TV off air due to jamming from Eritrean government



በኢንተርቴንመንት ላይ ያተኮረዉ የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ስርጭት ከአረብሳት እንዲወርድ ተገደደ !!
በዩተልሳት 7 ዌስት ( EUTELSAT 7W) በድጋሚ ስርጭቱን በኢትዮጵያ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ አገራት ማቅረብ መቀጠሉን ገለፀ!

ጥቅምት 21, 2005 (November 1,2012)

ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ በማደረግ በ2001 (በ2008 እ.ኤ.አ) በቴሌቪዥን ስርጭትና ፕሮግራም አቅርቦት የግል ኩባንያነት የተቋቋመ አለምአቀፍ የቴሌቭዥን ስርጭት ሲሆን በመስከረም 2003(SEPTEMBER 2010) በአለም ዙሪያ በጋላክሲ 19 እና አረብ ሳት ስርጭቱን በኢትዮጵያ ፣ በመካከለኛዉ ምስራቅ ፣ በአውሮፓ አገራት እና አሜሪካ በማድረግ ሲያሰራጭ ሁለተኛ አመቱን ይዟል፡፡

ኢ.ቢ.ኤስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በብሮድካስት ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀምና ቀልጣፋ አሰራር በመከተል አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በማቅረብ በአለም ዙሪያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ለማፍራት ችሏል፡፡
ይሁን እንጂ የአረብ ሳት የሳተላይት ኩባንያ መስከረም 15,2005 (September 25,2012) የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ስርጭትን ያለምንም ማስጠንቀቅያ ከሳተላይት ከማውረዱም በላይ የእርምጃው መንስኤ ከደቡባዊ የኤርትራ ምድር አቅጣጫ በተላከ የሳተላይት ሲግናል ማዛባትና እቀባ ወይም “ጃሚንግ” ምክንያት መሆኑን ገልፅዋል::



የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ጉዳዩ ከጠበቀው ቴክኒካዊ ችግር በላይ በመሆኑና የጉዳዩን ክብደት በመረዳት በትእግስትና በጥሞና በመከታተል እንዲሁም ይመለከታቸዋል ያላቸውን ባለድርሻ አካላት በማነጋገር ችግሩን በአግባቡ ለመፍታት ሐላፊነት በተሞላው መንገድ ሲንቀሳቀስ ቆይቷዋል:: የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት በዚህ ሳቢያ በተከሰተው አለመግባባትና ከአረብሳት ለማግኘት የጠየቀውን ተጨባጭ ማስረጃ ሳያገኝ በማናቸውም ወገኖች ላይ ውንጀላ ሳያቀርብ ለ25 ቀናት ስርጭታችን እንደተቋረጠ ለመቆየት ተገዷል::

የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት ጣቢያችን ለ25 ቀናት ተቋርጦ የነበረው ስርጭቱ እንዲመለስ ከብዙ ድርድር ና ክርክር በኋላ ጥቅምት 7,2005 (October 17,2012) ወደ መደበኛ የአየር ስርጭቱ እንዲመለስ ለማድረግ ቢችልም ፣ በሚያሳዝንና ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ አየር በተመልሰን በሶስት ቀናት ውስጥ አረብ ሳት ከኤርትራ ደረሰብኝ ባለው የሲግናል መዛባት እና ቀረበብኝ ባለዉ አቤቱታ ምክንያት ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ከሳተላይት ስርጭታችንን ሊያቋርጥብን ችሏል:: ሁለተኛውን እርምጃ ለየት የሚያደርገው የአረብሳት ከኤርትራ መንግስት የኢንፎርሜሽን መስርያ ቤት የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ስርጭት ከአረብሳት እንዲቋረጥ ተፅፎ ተላከልኝ ባለው ደብዳቤ ላይ ተመስርቶ በድጋሚ ስርጭታችንን ማቋረጡ ነው::

የአቤቱታ ደብዳቤው መሰረተ ሃሳብ የኢቢኤስ ፕሮግራሞችን ሁሉንአቀፍ የአስተማሪነትና የአዝናኝነት ሚና በመካድ በደፈናው ግጭትን የሚቀሰቅሱ አሉታዊ ፕሮግራሞችን ያቀርባል የሚል ነው:: ይሁን እንጂ ኢ.ቢ.ኤስ ይህ አቤቱታ መሰረተቢስ መሆኑን ለአረብሳት ደጋግሞ ከማሳወቁም ባሻገር የቴሌቪዥን ጣቢያችን በአሜሪካ ህግ የተቋቋመ የግል የቴሌቪዥን ኩባንያ ከመሆኑም በላይ ፓለቲካዊ ይዘት ላላቸው ዜናዎችም ሆኑ ፕሮግራሞች ትኩረት የሌለው መሆኑንና ባለፉት ሁለት አመታት ከማናቸውም ሃገራት ፣ መንግስታትና ቡድኖች ምንም አይነት አቤቱታ የቀረበበት አለመሆኑን፤ ከማናቸውም ወገኖች ጋር በሰላም የመስራት አላማ ያለዉ መሆኑን ገልፆ ሁሉም አካላት እንዲረዱ ጥረት አድርጓል::

ዛሬ በአለማችን በሶስተኛ ወገን በሚፈፀም የሳተላይት ሲግናል ማዛባትና እቀባ ወይም “ጃሚንግ” በርካታ አለማቀፍ ብሮድካስተሮችና ሃገራት ሲያማርሩ የሚሰማበት ወቅት ላይ የደረስን ቢሆንም በኢ.ቢ.ኤስ ላይ የደረሰው እቀባ በጃሚንግ ታሪክ በኢንተርቴንመንት ና ቢዝነስ ላይ ያተኮረ የቲቪ ስርጭት ከሳተላይት እንዲወርድ ሲደረግ የመጀመሪያው ነዉ፡፡ ይህን መሰል ህጋዊ ያልሆነ እርምጃ ትልቅ አለማቀፍ ህግና ጥበቃ የሚያሻ የኢንፎርሜሽን ዘመን ላይ መድረሳችንን ያሳያል::የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት በሁሉም የሳተላይት ተጠቃሚዎች ረገድ ሊኖር የሚገባውን መግባባትና የኢንፎርሜሽን ልውውጥ ወደፊት ተመሳሳይ ችግሮች ቢደርሱ ምን መደረግ አለበት በሚለው አነጋጋሪ ጉዳይ ላይ ከማናቸውም ወገኖች ጋር መፍትሄ ለማፈላለግ ጥረቱን ይቀጥላል::

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት በኢትዮጵያ ፣ በመካከለኛዉ ምስራቅ አገራት ለሚከታተሉን ውድ ተመልካቾቻችን በስርጭታችን መቋረጥ ለተፈጠረ ችግር ይቅርታችሁን እየጠየቅን ስርጭታችንን በአዲስ የሳተላይት መስመር ከዛሬ ጥቅምት 22,2005 (November 1,2012) ጀምሮ ዩተልሳት ከተባለው የአውሮፓ የሳተላይት ማሰራጫ ድርጅት ጋር ባደረግነው ውል ‘በዩተልሳት 7 ዌስት’ የስርጭት መስመር በፍሪኩዌንሲ 10815 (EUTELSAT 7W, Frequency 10815) ለማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን:: ቀደም ሲል የዲሽ አንቴናችሁን በናይልሳት መስመር ያደረጋችሁ ወይም የናይልሳትን የሳተላይት ስርጭቶች የምትከታተሉ ተመልካቾቻችን ያለምንም ችግር የጣቢያ ማፈላለጊያውን (ሪሞት ኮንትሮል) በ“ሰርች” ላይ በማኖር ራሱ ፈልጎ የሚያመጣልዎ መሆኑን እናሳዉቃለን:: በአሜሪካና በካናዳ ለሚኖሩ ተመልካቾቻችን በጋላክሲ 19 (Galaxy 19 at 97 degrees, freq.12177 V. TP 27, SID 23000) ስርጭታችን እንደቀጠለ መሆኑን እናስታውሳለን:: በዚህ ወቅት ከጎናችን በመቆም በምክርና በሃሳብ ላልተለያቹሁን ውድ ተመልካቾቻችን ፤ የቢዝነስና የፕሮግራም አጋሮቻችን ምስጋናችንን እያቀረብን በተከታታይ በተሻለ ስርጭትና ዝግጅት እያዝናኑ የሚያሳውቁ ፕሮግራሞቻችንን ማቅረባችንን የምንቀጥል መሆኑን እንገልፃለን::

የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን አለምአቀፍ ማኔጅመንት

Press Release:

On September 22, 2012, ARABSAT took EBS (ETHIOPIAN BROADCASTING SERVICE) off the air without any warning or notice due to alleged deliberate jamming of satellite signals from Eritrea.

Eritrea’s Ministry of Information reached out to ARABSAT and requested EBS to be removed from the platform, alleging “EBS’s destructive content consciously targets Eritrea and attempts to instigate conflict.”

Apart from these groundless and generalized allegations cited herein, it did not point to a specific instance of any wrongdoing by EBS. EBS worked vigorously to address any and all concerns raised by ARABSAT to no avail.

Since EBS is purely an entertainment channel, which does not foray into politics, EBS believed the allegations in the letter lacked credibility and advised ARABSAT as such. Despite EBS’s best efforts, ARABSAT unilaterally took EBS off the air a second time in late October, again without notice. EBS has begun plans for re-launch on a different satellite platform.

EBS TV Now available on Eutelsat 7W

Starting November 1, 2012 EBS is now available on Eutelsat 7W. We apologize to our viewers for any inconvenience this issue may have caused. Viewers that have experienced interruption of our transmission in the Middle East and Africa can now reposition their Satellite dish to Eutelsat 7W, same direction as Nilesat, and can continue to enjoy their favorite EBS Shows once again.
http://ebstv.tv/

No comments:

Post a Comment