Thursday, November 8, 2012

Colours of the Nile International Film Festival በአዲስ አበባ

ለሁለት ቀናት ብቻ አዲስ አበባ የመጣው ሴኔጋላዊው ፀሃፊ እና ዳይሬክተር ALAIN GOMIS 
ወጣቱ ሴኔጋላዊ  Satché (Saul Williams) ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ቀኑ እንደ ዘወትሩ አልነበረም፡፡ተጫጭኖታል፡፡ዘመድ አዝማድ እና ቤተሰቦቹ ይላቀሳሉ፡፡በምድር የሚኖርበት የመጨረሻ ቀን መሆኑ ተነገረው፡፡ለመሞት መመረጡ እንጂ ከዚህ የዘለለ ግልፅ ምክንያት የለም፡፡ቢሆንም በታሪኩ ፍሰትም ሆነ አወቃቀር ላይ አንዳች ተፅእኖ አይፈጥርም፡፡

ይህ ፊልም የሴኔጋላዊው ፀሃፊ እና ዳይሬክተር ALAIN GOMIS  TEY / TODAY ነው፡፡የTEY / TODAY ፊልም ዋና ገፀ ባህሪ Satché (Saul Williams) በህይወት በሚኖርባ የመጨረሻ ቀን በሴኔጋል ጎዳናዎች በሃገሩ ሰዎች ይሸኛል፡፡እርሱ እና አገሬው የሞቱን እውነትነት አምነው ተቀብለዋል፡፡
TEY / TODAY
Satché (Saul Williams) ስለሚለያቸው ሃዘናቸው ቢከፋም ለጀግንነቱ እና ስለ ፍቅራቸው ያላቸውን ሁሉ በስጦታ ያበረክታሉ፡፡ሁሉም….ህፃን…ወጣት…አዋቂ…ጎልማሳ …ሽማግሌ…ወንድ ሳይሉ ሴት፡፡Satché (Saul Williams) አገሬው ካደረገለት  ስንብት በኋላ ወደ ራሱ ይመለሳል፡፡በህይወቱ የመጨረሻ ቀን ማንን ማግኘት ምንስ ማድረግ ይፈልጋ፡፡ስሜትን ቆንጥጦ የሚይዝ ቆንጆ አፍሪካዊ ፊልም፡፡ተወልዶ ባደገባት ከተማ በህይወቱ ብቅ ጥልቅ ወዳሉት እና ወደሚሉት ሴኔጋላውያን ያመራል፡፡ከቀድሞ ፍቅረኛው  እስከ ብልሁ አጎቱ ድረስ፡፡ቀድሞ ልብ ያላላቸውን ነገሮች እያስተዋለ፤ጆ ያልሰጣቸውን ከልቡ እያደመጠ ናቃቸውን እየተመሰጠ  የመጨረሻ ቀኑን ሲኖር ሀገሩ ግን እንደ ሞተ ያህል ቆጥሮት ያዝንለታል፡፡ይህ የስሜት ውጣ ውረድ ቅደም ተከተላቸው በጠበቁ ምስሎች እና በርካታ የድምፅ ግብዓቶች የታጀበ ነው፡፡ፊልሙን ከጀመሩ ወዴትም መሄድ አይቻልም፡፡መጨረሻው ይናፍቃል፡፡

ይህ ግን ለኢትዮጵያውያን በተለይም ለአዲስ አቤዎች እጅጉን የተመቸ አይመስልም፡፡ሪባን ሲቆረጥ ያጨበጨበው ተመልካች የፊልሙን የመጀመሪያ  አስር ደቂቃዎች መመልከት በቂ ነው፡፡ከዚያ ብዙ የብሄራዊ ቴአትር ወንበሮች ባዶ ሆኑ፡፡

ይህ የALAIN GOMIS ፊልም ከሞት በጥቂት ርቀት ላይ የሚኖሩ አፍሪካውያንን ህይወት በእለተ ሞታቸው ቢያውቁ የሚኖራቸውን የስሜት ምስቅልቅል ይተርካል፡፡ ለSatché (Saul Williams) ሞት የሚኖርባት ከተማ አመራሮች ሽኝት ያደርጋሉ፡፡በስሙ ደግሰው ይገባበዛሉ፡፡ነገር ግን Satché (Saul Williams) በሞቱ በተደገሰው ድግስ ጉሮሮውን የሚያረጥብበት ጠብታ ነገር ለማግኘት ይቸገራል፡፡
Colours of the Nile International Film Festival በአዲስ አበባ
የአብረሃም ገዛኸኝ የሎሚ ሽታ
ይህ የፊልም ፌስቲቫል በኢትዮጵያዊው ፊልም ባለሙያ አብርሃም ሃይሌ እና Alla Verlotsky የተፈጠረ ነው፡፡ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን እስከ ህዳር 2 ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
በእነዚህ ቀናት በተለያዩ ዘርፎች ተሰሩ አፍሪካዊ ፊልሞች በፈረንሳይ እና ጣልያን የባህል ማዕከሎች ለእይታ ይበቃሉ፡፡በ Feature ፤ዘጋቢ (Documentary)፤አጫጭር (Shorts)የፊልም ዘውጎች ውድድሮች ይደረጋሉ፡፡የአብረሃም ገዛኸኝ የሎሚ ሽታ በውድድሩ ከሚሳተፉት አንዱ ነው፡፡

ክላውድ ሆፈር(Claude Haffner)
በዚህ ፊልም ፌስቲቫል የሚሳተፉት የፊልም ባለሙያዎች በአህጉሪቱ አንቱ የተባሉ ናቸው፡፡የፌስቲቫሉ አዘጋጆች ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ለሚገኘው የኢትዮጵያ የፊልም ኢንደስትሪ የሚበጅ ሃሳብ ይዘውም መተዋል፡፡
የፊልም ባለሙያዎቹ እውቀት እና ክህሎታቸውን የሚያገሩበት ሙያዊ የውይይት መድረኮች አሉ፡፡
ከእነዚህም መካከል እሁድ ህዳር 1 ቀን የፈረንሳይ እና ኮንጎ ጥምር ዜግነት ያላት  የዘጋቢ ፊልም ፕሮዲውሰር ክላውድ ሆፈር(Claude Haffner) የምትሳተፍበት መድረክ በጣሊያን የባህል ማዕከል ተዘጋጅቷል፡፡በመድረኩ የሴት የፊልም ባለሙያዎች ፈተና በአፍሪካ፤ሴትነት በፊልም ኢንደስትሪ፤የሴት እና ወንዶች የፊልም ታሪኮች እና አተያዮች፤በፊልም ኢንደስትሪ ውስጥ የሴቶች እድል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡
የአብርሃም ስጋት


ታህሳስ 28/2005 በብሄራዊ ቴአትር በተከፈተው የፊልም ፌስቲቫል በርካታ የኢትዮጵያ ዳይሬክተሮች፤ፕሮዲውሰሮች፤ተዋንያን እና ፀሃፊያን ተገኝተዋል፡፡
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ከ28 ሃገራት የተውጣጡትን የፊልም ባለሙያዎች እና የፌስቲቫሉን ፕሮግራሞች ሲያስተዋውቅ የነበረው አብርሃም ሀይሌ በአንድ ጉዳይ ሃሳብ ገብቶታል፡፡አደራችሁን አዳራሾቹ ባዶ ሆነው እንዳታሳፍሩኝ፡፡ይህ ስጋት ከምንም የመነጨ አልነበረም፡፡የኢትዮጵያ የፊልም ተመልካች ሮማንስ/ኮሜዲ በሚል የጀማሪዎች እና ደፋሮች ስራዎች ዥንጉርጉር ሆኗል፡፡በአማርኛ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ እምብዛም ተናጋሪ በሌላቸው የፈረንሳይኛ እና ፖርቹጊዝን  በመሳሰሉ ቋንቋዎች የተሰሩ ናቸው፡፡ለእነዚህ ፊልሞች ኢትዮጵያዊ ተመልካች ይጠፋ ይሆን የሚለው ስጋት አብርሃም ብቻ ሳይሆን እኔም እጋራዋለሁ፡፡
የፊልም ፌስቲቫሉ የአፍሪካውያንን ፊልም ለአፍሪካውያን ማስተዋወቅ እና የአህጉሪቱን የፊልም ኢንደስትሪ የማሳደግ አላማ አንግቧል፡፡