Wednesday, August 17, 2011

የአይዶል ምርጦች ታወቁ

• የኦፔራ አቀንቃኟ ሕፃን አንደኛ ሆነች

(ሪፖርተር) ሃና በልዩ ዘርፍ አንደኛ ብትባልም በዝግጅቱ ላይ ከኦፔራ በተጨማሪ እንደሌሎቹ ተወዳዳሪዎች የአንዲት ታዋቂ ድምፃዊትን ዜማ እንድትጫወት ተደርጐ ነበር፡፡ በዚህም በኦፔራ ብቻ ሳይሆን የአገራችንን ዜማዎች የመጫወት ብቃት እንዳላት አስመስክራለች፡፡ በዝግጅቱ ላይ የሕፃኗን ኦፔራ የመጫወት ብቃት ተመልካቹ በንጽጽር እንዲረዳ ከመድረኩ በቴፕ የኦፔራ ሙዚቃ እንዲለቀቅና ጐን ለጐን እሷ ኦፔራ እንድትጫወት የተደረገበት ሁኔታ ነበር፡፡

በዳንስና በባህላዊ ውዝዋዜ ቻዴት የባህል ቡድን፣ ሀሁ የዘመናዊ ዳንስ ቡድን እና የማይክል ጃክሰንን ዳንስ ይዞ የቀረበው ወጣት ታምራት ወደ ፍጻሜው የውድድር ዙር አልፈዋል፡፡

በዘፈን ወደ መጨረሻው ዙር ውድድር ያለፉት ምርጥ የአይዶል አምስቶች ዮሐና በላይ፣ ሐሰን አርጋው፣ ማስተዋል እያዩ፣ ይድነቃቸው በላይና ተመስገን ናቸው፡፡

ምንም እንኳን ለፍጻሜው ዙር ባይደርሱም ምርጥ አሥር ውስጥ የገቡ ተወዳዳሪዎች የፍጻሜ ውድድር በሚካሔድበት የነሐሴ 29 ቀን 2003 ዓ.ም. የኢትዮጵያን አይዶል ልዩ ዝግጅት ላይ ተገኝተው የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እንደሚቀበሉ የኢትዮጵያ አይዶል አስታውቋል፡፡

ተወዳዳሪዎች እስከዛሬ በተለያዩ ዙሮች ይሆነናል እንፈልገዋለን ያሉትን ዜማ ይዘው መቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ለፍጻሜው ዙር ግን በዳኞች በተመረጠላቸው ሥራ እንደሚቀርቡ የኢትዮጵያ አይዶል አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment