Wednesday, May 22, 2013

አያት አክሲዮን ማኅበር ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት ተወሰነበት


-    የማኅበሩ አመራሮችም በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ
-    አያት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይና የኮንስትራክሽን መሣርያዎች እንዲወረሱበት ተወስኗል

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተመሠረቱባቸው 23 ክሶች ለሦስት ዓመታት ከተከራከሩ በኋላ በቅርቡ በ21 ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት አያት አክሲዮን ማኅበርና ሦስት አመራሮች፣ በዛሬው ዕለት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትና ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ አያት አክሲዮን ማኅበር 90,091,270 ብር ቅጣት ሲወሰንበት፣ የማኅበሩ ከፍተኛ ባለድርሻና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ 12 ዓመት ፅኑ እስራትና 3,235,543.50 ብር ቅጣት፣ የኢንቨስትመንት ዳይሬክተሩ ዶ/ር መሐሪ መኮንን 12 ዓመት ፅኑ እስራትና 436,646.60 ብር ቅጣት፣ የፋይናንስ ኃላፊው አቶ ጌታቸው አጎናፍር 10 ዓመት ፅኑ እስራትና 411,969.60 ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ አያት አክሲዮን ማኅበር የባንክና የኢንሹራንስ ሥራዎችን ተክቶ በመሥራት፣ አራጣ በማበደርና መሰል ተግባራት ውስጥ በመሳተፉ 86,495,726 ብር እንዲወረስበት ፍርድ ቤቱ መወሰኑን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም አቶ አያሌው ተሰማና አያት አክሲዮን ማኅበር በጋራ ጥፋተኛ በተባሉበት ሌላ ክስ ከቀረጥ ነፃ የገቡ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች እንዲወረሱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/

No comments:

Post a Comment