Thursday, May 16, 2013

ድምጻዊት አበበች ደራራ ከዚህ አለም በሞት ተለየች



ድምጻዊት አበበች ደራራ ከዚህ አለም በሞት መለየቷን የተለያዩ ድረ ገፆች እየዘገቡ ነው፡፡  ማለዳ ታይምስ ድረ ገፅ ድምጻዊት አበበች ደራራ በስደት አለም እስራኤል አገር ውስጥ በቴል አቪቭ ከተማ ኑሮዋን ካደረገችበት ጊዜ ጀምሮ በጤና መታወክ ለብዙ ጊዜ ስትሰቃይ መክረሟን ገልጾ በዛሬው እለት ህይወቷ ማለፉን እና የቀብር ስነስራቷ በእዚያው በቴል አቪቭ እንደሚፈጸም ጠቁሞአል ።በተለይም ባሳልፍነው ስድስት ወራት ህመሟ በከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች ከመገለጹም በላይ ለህክምና እርዳታ የሚሆናትን ገንዘብ እንዲሰባሰብ በተለያዩ አገራት ላይ እንዲከናወን መጠየቁ ይታወሳል ።ሆኖም ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ ሲደረግ እንዳልታየ የሚታወቅ ነው አበበች ደራራ በራስ ቴአትር ሃገረሰብ የተሰኘ ቡደን በተቋቋመበት ወቅት ከነ ነዋይ ደበበ ጋር በመሆን በማቋቋም ስራዋን በከፍተኛ ደረጃ የጀመረች ድንቅ አርቲስት ነበርች በተለይም በመድረክ ላይ እንቅስቃሴዋ የሰውን ቀልብ ትስባለች እየተባለ የምትወደሰው ድምጻዊት ደራራ የራስ ቴአትር አምባሳደር ትባልም እንደነበር ያገኘነው ፋይል ይጠቁማል።በቴአትር ቤቶች ውስጥ በመድረቅ የሙዚቃ ስራን በመስራት ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈች ሲሆን ጥቂት የማይባሉ ሙዚቃዎችንም በካሴት አሳትማ ልህዝብ አቅርባለች ከነዚህም መካከል በሉ እንጂ ፣ተው ማነህ፣ገላዬ ፣ሰው በፍቅር ታሞ የተባሉት ጥቂቶቹ ናቸው አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3.00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም እንደሚከናወን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment