Thursday, January 26, 2012

ሰበር ዜና ፦ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ ኤልያስ ክፍሌ ተፈረደባቸው


የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጥር 17 ቀን 2004 .. በዋለው ችሎት በአምስት የሽብር ወንጀል ተከሳሾች ላይ ከዕድሜ ልክ እስከ 19 ዓመትና የገንዘብ ቅጣት ወሰነ፡፡ በዚህ መሠረት ኤልያስ ክፍሌ የዕድሜ ልክ እስራት የተወሰነበት ሲሆን፣ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር 17 ዓመት እስራትና 50 ሺሕ ብር ቅጣት፣ ውብሸት ታዬ 14 ዓመት እስራትና 33 ሺሕ ብር ቅጣት፣ ሒሩት ክፍሌ 19 ዓመት እስራት፣ ርዕዮት ዓለሙ 14 ዓመት እስራትና 36 ሺሕ ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡

አምስቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው ለአምስት ዓመታት ከሕዝባዊ መብቶቻቸው እንዲታገዱ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡