Thursday, January 19, 2012

ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰለች መልካሙን ጨምሮ 35 አትሌቶች ከአለም አቀፍ ውድድሮች ታገዱ


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ለለንደን ኦሎምፒክ ዝግጅት በስልጥና ላይ ሳይገኙ የቀሩ 35 አትሌቶችን ከአለም አቀፍ ውድድሮች ማገዱን አስታወቀ፡፡


ፌደሬሽኑ ካገዳቸው 17 የአምስት ሺህ እና 5 የአስር ሺህ ሜትር አትሌቶች መካከል ታዋቂዎቹ ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን፣ አየለ አብሽሮ፣ ሁነኛው መስፍን፣ ጥላሁን ረጋሳ፣ ሌሊሳ ደሲሳ፣ ዲኖ ስፍር፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰለች መልካሙ እና ውዴ አያሌው ይገኙበታል፡፡

በማራቶን ወንዶች አብረሃም ጨርቆሴ፣ በሴቶች ማሚቱ ዳስካ፣ ቲኪ ገላና፣ ኮረኒ ጀሊላ፣ ብዙነሽ በቀለ እና አበሩ ከበደ ይጠቀሳሉ፡፡

1500 ሜትር አትሌት ቃልኪዳን ገዛኀኝ እና ትዝታ ቦጋለ፤ 3000 ሜትር መሰናክል እቴነሽ ዲሮ፣ መቅደስ በቀለ እና ህይወት አያሌው ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ለለንደን ኦሎምፒክ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ 223 አትሌቶችን መርጦ ከአንድ ወር በፊት ዝግጅት መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ፌደሬሽኑ የአሰልጣኝነት ፍቃዳቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቋቸው ማስረጃዎቻቸውን ሳያቀርቡ በቀሩ ስድስት የማናጀር ተወካዮችና አሰልጣኞች ላይም እገዳ መጣሉን ፌደሬሽኑ በተለይ ለኢሬቴድ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቀጣይም በመሰል ተግባራት በሚሰማሩ ላይ ሁሉ ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የፌደሬሽኑ ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment