Wednesday, January 18, 2012

አፋር ውስጥ አምስት የውጭ ቱሪስቶች ተገደሉ


•    በሽፍቶች የተወሰዱ አሉ ተብሏል

በአፋር ክልል በበረሃይሌ ወረዳ ኤርታኤሌ አካባቢ በጉብኝት ላይ ከነበሩ ስምንት የውጭ ቱሪስቶች መካከል፣ አምስቱ ባለፈው ሰኞ ሌሊት መገደላቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በጉብኝት ላይ በነበሩት ስምንት የውጭ አገር ጐብኝዎች፣ አስጐብኝዎችና ታጣቂዎች ላይ ተኩስ የከፈቱት የኤርትራ ታጣቂ ሽፍቶች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ምንጮቹ ገልጸው፣ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከውጭ ዜጐች መካከል አምስቱ ሲገደሉ፣ ሁለቱ ቆስለው ሲተርፉ አንዷ ግን ምንም ሳይደርስባት መትረፏን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

ሽፍቶቹ አስጐብኝውንና ለቱሪስቶቹ ጥበቃ የሚያደርጉ ታጣቂዎችን (ቁጥራቸው አልታወቀም) ይዘዋቸው ሳይሄዱ እንዳልቀሩም ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

ሕይወታቸው ያለፉትን አምስት የውጭ አገር ዜጐች አስከሬንና ሕይወታቸው የተረፈውን በአፍዴራ በኩል ትናንት ሌሊቱን ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት፣ ሔሊኮፕተሮች ወደ ሥፍራው መሄዳቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው በአሁኑ ጊዜ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት አባላት በመግባታቸው፣ ጥበቃውም ሆነ የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ መሆኑን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

No comments:

Post a Comment