Posted by Matias Estifanos on sodere.com
ዕረቡ ጳጉሜ 3 ቀን 2003 ዓ.ም
አዲሱ ዓመት በኢንተርናሽናል ግጥሚያ ነው የሚከፈተው፡፡ ሴቶቹ ዱቡብ አፍሪካን ይገጥማሉ፡፡ ስታዲየሙን ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ ከተላንት በስቲያ መልበሻ ክፍሉን ሲጎበኙት ነበር፡፡ ቀለም መቀባት አለበት ብለው ሲነጋገሩ ሰማሁ፡፡ ምንድነው ብዬ ስጠይቅ ለደቡብ አፍሪካ ነው አሉኝ፡፡ ጉዳዩን ሳጣራ ቀለም መቀባቱ በራሱ ከነዚያ አንፀር የሚሰቀጥጥና አናሳ ነገር ነው፡፡ ጉዳዩ የመስተንግዶ ክብደት ነው፡፡ እንዳንዋረድ አይነት ሆኖ ‹‹ እኛስ ምን እናድርግላቸው?›› የኛ ቡድን ደቡብ አፍረካ በሄደ ጊዜ መልበሻ ክፍሉ የተለየ ነው፡፡ ለያንዳንዱ ተጨዋች የራሱ ሳጥን አለው፡፣ መቀመጫ አለው፣ ፎጣ፣ ሳሙና፣ ነጠላ ጫማ፣ ልዩ መዋቢያ ቅባቶች አሉት ፡፡ ይህ መልበሻ ክፍሉ ነው፡፡ የሚቀጥለው ደግሞ መታሻ ክፍል ነው ተጨዋቾቹ ማሳጅ እዲያደርጉ ከመኝታው ጀምሮ የህክምና ቁሳቁሶች ያገኛሉ፡፡ ሶስተኛው ቦታ ደግሞ ፈሳሽ ነገሮችን የሚጠቀሙበት ነው ፡፡ በዚያ ክፍል ከሻይ ቡና ጀምሮ ልዩ ልዩ ውሃዎች በፊፋ የተፈቀዱ ኃይል ሰጪዎች ወተትና የፍራፍሬ ጭማቂዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ በነፃ ነው 㜎ሚቀመጡት፡፡ ተጨዋቾቹ ይህንን ሲያዩ ልደት እንጂ ግጥሚያ አልመሰላቸውም፡፡ በልበሻ ክፍል ሳይሆን ቤተመንግስት ነው የመሰላቸው ፡፡ የኛ ተጨዋቾችና ሀላፊዎች መልበሻ ክፍሉን ሲያያ በጣም ነው ያሳፈራቸው፡፡ ያፈሩት የኛ መልበሻ ክፍል ተብዬ ምን እንደሆነ ሲያስቡት ነው፡፡ ይህ ስታዲየም አለም ዋንጫን ያላስተናገደ ዝቅተኛ የሚባል ነው፡፡ የኛ ሰዎች ለጉብኝት ድሆች መንደር ያለ በጠም የደከመና ዝቅጠኛ ስታዲየም ሄደው ጎበኙ፡፡ ይህ ደካማ የተባለው ስታዲያም ጅምናዚያም ያለው፣ ትልቅ ካፍቴሪያ፣ ንፁ መልበሻ ክፍሉን ሲያዩት በጣም ነው የተገረሙት፡፡ የኛ ትልቁ ስታዲየም ግን መልበሻ ክፍል ውስጥ አንድ አግዳሚ አለ፡፡ እኔ ተጨዋች በነበርኩበት ጊዜ የማውቀው ይመስለኛል፡፡ ግርግዳው ተላልጦ ከላይ የሚወርደው ውሃ ሰነጣጥቆት መስመር ሰርተለታል፡፡ ይህ መልበሻ ክፍል ከተሰራ 50 ዓመት ያህል ሆኖታል፡፡ አሁን ግርግዳው ስለተሰነጣጠቀ ደቡብ አፍሪካ ለመቀበል ሽማግሌው መልበሻ ክፍል ፀጉሩን ቀለም ሊቀባ ነው፡፡ መልበሻ ክፍሉ ለደቡብ አፍሪካ ነው የሚታደሰው፡፡ ለተመልካቹም መጸዳጃ ክፍሉ ሊታደስለት ታስበዋል?፡፡ ሽንትቤቱን በተመለከተ በምን መንገድ መስተካከል እንዳለበት የተለየ ሀሳብ ካላችሁ እንደዚህ ይደረግ በሚል ሀሳብ ስጡ፡፡ እኔ ለማጠቃለል አንድ ነገር ላጫውታችሁ፡፡ በ1950 ስታዲየሙ በቆርቆሮ ነው የታጠረው ጊቢው ውስጥ መልበሻ ክፍል፣ ሽንት ቤት የሚባል ነገር የለውም፡፡ እረፍት በሚሆን ሰዓት ለመፀዳዳት የሚፈልግ ተቆጥሮ ወደ ውጪ ይወጣል፡፡ አካባቢው ጫካ ነው፡፡ በአንደኛው በር 20 ተቆጥረው ከወጡ ተጸዳድተው ይጨርሱና ይሰለፋሉ፡፡ 20 መሆናቸው ይቆጠራል፡፡ 21 ቢሆኑ እንኳን የመጨረሻው ሰው ይወጣል፡፡ ስለዚህ ሰልፈኞቹ ጣልቃ አያስገቡም፡፡ ያን ጊዜ እንደዚህ ነበር፡፡ አሁን ሽንትቤቱ ማፅዳት ካልተቻለ የበፊቱን መንገድ መከተል ነው የሚሻለው….፡፡
http://sodere.com
No comments:
Post a Comment