አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል የተባለውና ዜድቲኢ በተባለው የቻይና የመንግሥት ኩባንያ የተዘረጋው የቴሌኮም ኔትወርክ፣ አሁን ካለው ኔትወርክ ጋር የሚዋሀደውና ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ላይ የሚውለው እ.ኤ.አ በ2012 መጨረሻ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡
አሁን ላለው ደካማ የኢንተርኔትና የቴሌኮም አገልግሎት ዋነኛ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ በቻይናው ኩባንያ የተዘረጋው ኔትወርክ ሙሉ በሙሉ አሁን በአገልግሎት ላይ ካለው ኔትወርክ ጋር ባለመዋሀዱ መሆኑን፣ የኢንፎርሜሽንና የኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈው ሳምንት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በዜድቲኢ የተዘረጋውን ኔትወርክን በተመለከተ ኢትዮ ቴሌኮም በየሳምንቱ ክትትል የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ሚሼል ላቲዩት፣ በአሁኑ ወቅት በድርጅቱ ጥብቅ ክትትል በ1.5 ቢሊዮን ዶላር የተዘረጋው ኔትወርክ በማገልገል ላይ ካለው ኔትወርክ ጋር እየተዋሀደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዜድቲኢ የተዘረጋው ኔትወርክ አሁን ካለው ኔትወርክ ጋር ሙሉ ለሙሉ ሲዋሀድ፣ አሁን ያለው የቴሌኮም አገልግሎት በእጅጉ እንደሚሻሻልም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
ሚስተር ላቲዩት ይህን የገለጹት ከትናንት በስቲያ ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን በኦፕቲካል ፋይበር ግራውንድ ዋየር የኪራይ ውል በሸራተን አዲስ ውል በተፈራረሙበት ወቅት ነው፡፡
የውል ስምምነቱ ለመጪዎቹ አሥራ አምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ በስምምነቱ ውስጥ የሚካተቱ በ13 የተለያዩ ዋና ዋና መስመሮች ውስጥ ያሉ 52 የኦፕቲካል ፋይበር መስመሮች ናቸው፡፡ በውሉ ከተካተቱት መስመሮች ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም 1,424 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ተረክቧል፡፡
ይኸው በሌሎች አገሮች ቀደም ሲል የተተገበረ አሠራር የሁለቱን የመንግሥት መሠረተ ልማት መሥሪያ ቤቶች የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮ ቴሌኮም በፋይበር ኦፕቲክስ አማካኝነት እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት የተሻለ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኮርፖሬሽን የተዘረጋውና የሚዘረጋው የፋይበር ግራውንድ ዋየር፣ በኢትዮ ቴሌኮም እንደተዘረጋው ፋይበር ኦፕቲክ ለመቆረጥ አደጋ የማይጋለጥ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የኦፕቲካል ፋይበር ግራውንድ ዋየር ኬብሎች በተፈጥሯቸው ከሌሎች መሬት ውስጥ ከሚቀበሩ የፋይበር ኬብሎች በተሻለ ሁኔታ አስተማማኝ ከመሆናቸውም ባሻገር፣ በመንገድ ኮንስትራክሽን፣ በሲቪል ሥራዎች፣ በመሬት መሸርሸርና ሆን ተብሎ በግለሰቦች ለሚደርሱ የተለያዩ አደጋዎች የመጋለጥ ዕድሉ ዝቅተኛ መሆኑ ተነግሯል፡፡
እያንዳንዱ የኦፕቲካል ፋይበር ግራውንድ ዋየር ከ12 እስከ 48 የፋይበር ኮሮች ያሉት ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ኮርፖሬሽኑ የተወሰኑትን መስመሮች ለትራንስሚሽንና ለኤሌክትሪክ ኃይል መሣሪያ መቆጣጠሪያ የሚጠቀምበት መሆኑም ተብራርቷል፡፡
ወደፊት በአገሪቱ ያለው የትራንስሚሽን ኔትወርክ በሙሉ ይህን ቴክኖሎጂ የሚያካትት እንደሚሆንም፣ ስምምነቱን ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር የተፈራረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ምህረት ደበበ ጠቁመዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የኦፕቲካል ፋይበር ግራውንድ ዋየር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ግልጋሎትና ስርጭትን ከግራውንዲንግና ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶች ጋር አጣምሮ ለመስጠት የሚያስችል የኬብል ሽቦ ዓይነት ነው፡፡
የኬብሉ አንዱ ገጽታ የተተከሉ ማማዎችን ግራውንድ ከማድረግ በተጨማሪ፣ ከፍተኛ ቮልቴጅ የሚሸከሙ ኮንዳክተሮችን ወይም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎችን ከመብረቅ የሚከላከል መሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም በኬብሉ ውስጣዊ ክፍል የሚገኙት ፋይበር ኬብሎች ከፍተኛ ፍጥነት ላለው የትራንስሚሽን ሥራ መዋል እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡

No comments:
Post a Comment