Sunday, July 31, 2011



(ሪፖርተር)
SUNDAY, 31 JULY 2011 00:00
BY TAMIRU TSIGE
·          
በአፍሪካ አኅጉር ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 19ኛው የዓለም ዋንጫ ከኢትዮጵያ ተመልካቾችን ለመላክ ተብሎ በተፈጠረ ማጭበርበር ምክንያት፣ ከህዳር 3 ቀን 2003 .. ጀምሮ በጀርመን ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የነበሩት የአስካሉካን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጡ፡፡
የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ የሰጣቸው የአስካሉካን ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ግርማይ ገብረ ሚካኤል፣ ሐምሌ 22 ቀን 2003 .. ከማለዳው 200 ሰዓት አካባቢ በኢንተርፖል አጃቢነት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን፣ የፌዴራል ፖሊስ ጊዜያዊ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር በቀለ ሀብቴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ወንጀለኛ የትም አገር ሄዶ አያመልጥም›› ያሉት ኮማንደር በቀለ፣ አቶ ግርማይ ተላልፈው ሊሰጡ የቻሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በፌዴራል ፖሊስ በተደረገ ጥረት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በግለሰቡ ላይ የክስ ሒደቱ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ አንድ ዲፕሎማት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑን ኤምባሲው በማሳወቁ፣ አቶ ግርማይ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡የአስካሉካን ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ግርማይ በአፍሪካ አኅጉር ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ መታደም ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በኤሌክትሮኒክስና በሕትመት መገናኛ ብዙኅን ባስተላለፉት ማስታወቂያ መሠረት 1,200 በላይ ዜጐችን ኩባንያቸው መዝግቧል፡፡ዜጐቹ ሲመዘገቡ እያንዳንዳቸው 37,582.85 ብር በድምሩ 45 ሚሊዮን ብር በላይ የከፈሉ ሲሆን፣ አቶ ግርማይ ትክክለኛ ቁጥራቸው ባይታወቅም የተወሰኑ ተመዝጋቢዎችን ከላኩ በኋላ ምን እንዳጋጠማቸውና ምክንያታቸውንም ሳያውቁ ይሰወራሉ፡፡የዓለምን ዋንጫ እስከ መጨረሻው እንደሚከታተሉ የተገለጸላቸው ከአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተለይ ከደቡብ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመጡ 1,200 በላይ የሚሆኑ ዜጐች፣ ደቡብ አፍሪካ ሳይጓዙ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጀምሮ ሳምንታት ማስቆጠር ሲጀምር መታለላቸው ስለገባቸው ተቃውሞአቸውን መግለጽ ጀመሩ፡፡ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ፖሊስ የአስካሉካን ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ (የአቶ ግርማይ ባለቤት) / መና ተረፈን፣ የድርጅቱን ገንዘብ ያዥ አቶ ግርማ በቀለን፣ የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊን አቶ ደረጀ ባዩንና በኤጀንትነት (ደላላ) ይሠሩ የነበሩትን አቶ ብርሃኑ ቤንጫሞን በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ የድርጅቱን ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ግርማይ እያፈላለገና ምርመራውን ሲያደርግ ቆይቶ የምርመራውን ውጤት ለዓቃቤ ሕግ አስተላለፈ፡፡የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ‹‹ቢፒአር ችሎት›› ሐምሌ 22 ቀን 2002 .. 19ኛውን የዓለም ዋንጫን ሽፋን በማድረግ 1,200 በላይ ዜጐችን ‹‹ወደ ደቡብ አፍሪካ ትሄዳላችሁ በማለት ወንጀል ፈጽመዋል›› ባላቸው በዋና ሥራ አስኪያጇ / መና ተረፈ፣ በገንዘብ ያዥው አቶ ግርማ በቀለ፣ በአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊው አቶ ደረጀ ባዩ፣ በኤጀንቱ (ደላላው) አቶ ብርሃኑ ቤንጫሞና በአስካሉካን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላይ ክስ መሠረተ፡፡ዓቃቤ ሕግ ክሱን መስርቶ ጉዳዩ በመታየት ላይ እያለ በተለይ ከክልሎች (ከደቡብ) መሬታቸውን፣ ቤታቸውን፣ ከብቶቻቸውንና የእርሻ ሰብላቸውን ሸጠው የከፈሉና ወደቀያቸው መመለሻ የሌላቸው በርካታ ዜጐች፣ ‹‹የክስ ሒደቱ ተጓተተ፣ ይፋጠን፣ የምንበላው የለንም ንብረቱ ይሸጥና ይሰጠን፣ በባንክ ያለው ገንዘብ ወጥቶ ይሰጠን፣ ወዘተ›› በማለት እየተቃወሙ ባሉበት ወቅት፣ አቶ ግርማይ ህዳር 20 ቀን 2003 .. በጀርመን አገር ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ፡፡ቁጥራቸው 100 በላይ የሚሆኑ ተበዳዮች የግለሰቡን መያዝ በሰሙ በሁለተኛው ቀን፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ በሠልፍ ሄደው የጀርመን መንግሥት ግለሰቡን አሳልፎ እንዲሰጥ ጠየቁ፡፡በወቅቱ የኤምባሲው ምክትል ካውንስለር ሚስተር ሚካኤል ቢኦንቲኖ ለተበዳዮቹ በሰጡት ምላሽ፣ ግለሰቡ የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቁ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ግለሰቡ የፖለቲካ ችግር እንደሌለባቸው መግለጹንና የግለሰቦችን ገንዘብ ይዘው መሰወራቸውን በማሳወቅ ተላልፈው እንዲሰጡት መጠየቁን አስታውቀዋቸዋል፡፡ በመቀጠልም ጉዳዩን የጀርመን መንግሥት እያጠናው እንደነበርም ነግረዋቸዋል፡፡ኢትዮጵያና ጀርመን ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ስላላቸው፣ ከስምንት ወራት በኋላ ሐምሌ 22 ቀን 2002 .. የአስካሉካን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ግርማይ ገብረ ሚካኤልን የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባቸው የነበሩት የአስካሉካን ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ / መናን ጨምሮ አራቱ የድርጅቱ ሠራተኞች እስከ አራት ዓመታት በሚደርስ እስራት መቀጣታቸውንና የድርጅቱ ንብረትና በባንክ የተገኘው ገንዘብ ለተበዳዮቹ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወሳል፡፡


No comments:

Post a Comment