Friday, September 16, 2011

Asnakech Worku dies at 78


አስናቀች በአዲስ አበባ ከተማ ገዳም ሰፈር አካባቢ በ1926 ተወለደች፡፡ገና በህጻንነቷ እናቷን በሞት የተነጠቀችው እና በክርስትና እናቷ ቤት ህይወትን በእንጉርጉሮ ዳዴ ማለት የጀመረችው አስናቀች በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ገብታ ለመማር ሙከራ ብታደርግም አልተሳካላትም፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መድረክ ብቅ ያለችው የፍቅር ጮራ በተሰኘ ቴአትር ነበር፡፡ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በበርካታ መድረኮች ተውናለች ክራር ደርድራለች፡፡ከ1955 እስከ 1980ዎቹ በቀድሞው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ትያትር ቤት አገልግላለች፡፡ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ ሃገሮች ስራዎቿን የማቅረብ እድልም ነበራት፡፡እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሴቶች የኪነ ጥበብ በዓል ላይ ተካፍላም ነበር፡፡አስናቀች ለዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆናም ነበር፡፡የተለያዩ ሰዎች እና የስራ ባልደረቦቿ እገዛ ሊያደርጉላት ቢሞክሩም የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ትናንት መስከረም 4 2004 ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች፡፡የቀብር ስነ ስርዓቱም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በአርበኞች መካነ መቃብር ተካሂዷል፡፡ለቤተሰቦቿ እና ለአድናቂዎቿ መፅናናት ይሁን፡፡

No comments:

Post a Comment