አደጋው የደረሰው ኮድ 3 አዲስ
አበባ የሰሌዳ ቁጥሩ 27 8 55 የሆነው የሚኒባስ ተሽከርካሪ
ከተፈቀደው የጭነት ልክ በላይ ዘጠኝ ትርፍ ሰዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።
ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት ሲጓዝ በሞጆ ከተማ
በብልሽት ከቆመ ማርቼዲስ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው።
በብልሽት ምክንያት የቆመው ተሽከርካሪም ከርቀት የሚያንፀባርቅ ምልክት አለማድረጉና በወቅቱ አለመነሳቱም
ለአደጋው ተጨማሪ ምክንያት ነው ተብሏል።
በአደጋው የሞቱ 16 ሰዎች አስከሬን በአዳማ ሆስፒታል ለጊዜው የገባ ሲሆን ከቆይታ በኋላም ማንነታቸውን በመለየት የሞቾችን አስከሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲውስዱ ተድርጓል፡፡
ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው
ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አዲስ አበባ መላካቸውንም የኢዜአ ዘገባ
አመልክቷል።
http://www.fanabc.com/
No comments:
Post a Comment