Wednesday, January 15, 2014

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወደ ኣገር ቤት ለመግባት መወሰኑን ኣስታወቀ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ «ኦ ዲ ኤፍ» ወደ ኣገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ኣስታወቀ። የግንባሩ ፕሬዝደንት አቶ ሌንጮ ለታ እንደገለጹት ግንባሩ ከምስረታው ኣንስቶ ወደ ኣገር ቤት ለመመለስ ግልጽ አቐም ይዟል። ለኢትዮጵያ ህዝቦች አዲስ ራዕይ ኣለኝ የሚለው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ መሰረት ያለው ኣገራዊ ኣንድነትን ለመመስረት እንደሚሰራም ኣስታውቐል።
«ኦ ዲ ኤፍ» በይፋ ከተመሰረተ ገና ኣንድ ዓመቱ ሲሆን ፕሬዝደንቱ አቶ ሌንጮ ለታ ለረጅም ጊዜ የዓማጺው ኦሮሞ ነጻነት ግንብር ከፍተኛ ዓመራር አባል እንደነበሩ ኣይዘነጋም።
http://www.dw.de

No comments:

Post a Comment