Sunday, October 16, 2011

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ቡድን መለስተኛ አውቶቡስ እና አንበሳ አውቶቡስ ተጋጩ


ትናንት ረፋዱ ላይ ከሎምባርዲያ ሬስቶራንት ወደ አራት ኪሎ ሲያመራ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ቡድን መለስተኛ አውቶቡስ የመገልበጥ አደጋ ደረሰበት፡፡
አደጋው የተከሰተው ኢትዮጵያ ሆቴል አጠገብ የባንኮች አውቶቡስ ከአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ጋር በደረሰበት ግጭት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባንክ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ጥላሁን መንገሻ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ በአደጋው ወቅት የቡድኑ 12 ተጫዋቾች አውቶቡሱ ውስጥ የነበሩ ሲሆን፣ በተጫዋቾች ላይ የከፋ ጉዳት አልደረሰም፡፡

በደረሰው የመገልበጥ አደጋ ምክንያት ተጫዋቾቹ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል የሕክምና ዕርዳታ ተደርጎላቸዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ቡድኖች ለአዲስ አበባ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያ ነበራቸው፡፡ ይሁንና በደረሰው አደጋ ምክንያት ግጥሚያው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ዘንድሮ በከተማው ውስጥ የትራፊክ አደጋ በጣም እየጨመረ መምጣቱን እየገለጸ ነው፡፡ በተለይ በመስከረም ወር የተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች በሰው ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጾ፣ የጥቅምት ወር ከተጀመረ ወዲህም በርካታ አደጋዎች በአሽከርካሪዎች ግድየለሽነት እየተከሰቱ ነው ብሏል፡፡ በምስሉ ላይ የሚታየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ቡድን አውቶቡስ በደረሰበት ግጭት ከተገለበጠ በኋላ ነው፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/

No comments:

Post a Comment