የአዲስ አበባ ስታዲየም እጅጉን ደመቅ ብሏል፡፡የቡና
ደጋፊዎች የደስታ ሁካታ በከተማዋ እምብርት በሚገኘው የአዲስ አበባ ስታዲም ደምቆ ይሰማል፡፡ባለፈው አመት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ያነሳው ኢትዮጵያ ቡና በኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የደርሶ መልስ ጨዋታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ
የነበረውን ግጥሚያ 0፡0 አጠናቆ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል፡፡ከቀናት በፊት ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና
2፡1 አሸንፎ ነበር፡፡ጨዋታው ሲጠናቀቅ በመልሱ ጨዋታ ቡናን እንደሚያሸንፉ ያለፈ ታሪክ አስታውሰው የተናገሩት የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ሃሳባቸው የሰመረ አይመስልም፡፡በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተወዳጅ
ከሆኑት የደርቢ ጨዋታዎች ቀዳሚው የሆነው የቡናና የጊዮርጊስ ጨዋታ ባለፈው ሳምንት ሲገናኙም የወትሮ መተነኳኮስ አልጠፋውም፡፡ በሳምንቱ
ጨዋታ ታፈሰ ተስፋዬ እና ሳሙኤል ታዬ ለኢትዮጵያ ቡና ሱሌይማ መሃመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡በእለቱ የቡናው አሰልጣኝ
በዳኝነቱ ክፉኛ መማረራቸውን ገልፀው ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ከእጁ ያስገባው ይህ ዋንጫ
የባለፈው አመት ሲሆን በመርሃግብሮች መጓተት ወደዚህኛው አመት የተሻገረ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment