አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋልያዎቹን ከሁለት አመት በላይ ሲያሰለጥኑ የቆዩትን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን ያሰናበተ ሲሆን ፥ ዛሬ በፅህፈት ቤቱ መግለጫ እንደሚሰጥም ነው የተነገረው።
ብሄራዊ ቡድኑ በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት ከጥር 3 ጀምሮ ለ20 ቀናት በተካሄደው የቻን ውድድር ላይ ተሳትፎ በሶስቱም የምድብ ጨዋታዎች በሊቢያ ፣ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና በጋና የተሸነፈ ሲሆን ፥በአንፃሩ አንድም ግብ ማስቆጠር ሳይችል ከውድድሩ በግዜ መሰናበቱ ይታወሳል።
አሰልጣኙ ከ31 ዓመታት በዃላ ብሄራዊ ቡድኑ በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት የተካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫን ትኬት እንዲቆርጥ አስችለውት የነበር ቢሆንም ፥ በቻን ውድድር ዋልያዎቹ የነበራቸው አቋም ብዙ ትችትን እንዲያስተናግዱ አድርጓል።
የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በቻን ውድድር ለተመዘገበው ውጤት ከጋዜጠኞች የሚደርስብን ትችት በሙሉ ትኩረት እንዳንጫወት የስነልቦና ጫና አሳድሮብናል ሲሉ አስተያየት መስጠታቸውም በብዙ የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ አልተወደደላቸውም ነበር ።
http://fanabc.com/

No comments:
Post a Comment