አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2005 የትምህርት ዘመን የ12 ክፍል የመሰናዶ ፈተናን ካለፉት 163ሺህ 406 ተማሪዎች መካከል 103 ሺህ 394 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል ።
ምደባው ዛሬ በአገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ኤጀንሲ የተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲ ድልደላ ተካሂዷል ።
ተማሪዎችም የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በኤጀንሲው ድረ ገፅ http://www.nae.gov.et/ በመግባት placement result የሚለውን በመጫን መመልከት ይችላሉ ።
ወይም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት plr ፅፎ የመለያ ቁጥርን በማስከተል ለ8181 በመላክ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ማወቅ የችላሉ ብሏል ኤጀንሲው ።
ምደባው የተከናወነው የ70/30 ቀመርን ባሟላ መልኩ ከጠቅላላ ተፈታኞች ደግሞ 40 በመቶዎቹ በምህንድስና ሳይንስ ዘርፍ እንዲገቡ ተደርጓል ።
በምደባው የሴቶችን ተሳትፍ 38 በመቶ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የተከናወነ ሲሆን ፥ የህክምና ሳይንስን ምርጫቸው ያደረጉ ተማሪዎች ደግሞ የመቁረጫ ነጥብን ለወንዶች 482 ለሴቶች ደግሞ 477 እንዲሆን ተደርጓል ።
የምደባ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የቅበላ አቅምን ታሳቢ ተደርጎ ሴት ተማሩዎች ከወንዶች ጋር ተወዳድረው ከሚያገኙት በተጨማሪ 3 በመቶ እርስ በርሳቸው ተወዳድረው ወደሚፈልጉት የትምህርት መስክ እንዲገቡ መደረጉን ነው ኤጀንሲው የገለፀው ።
የሚያጠቡ እናቶች በአቅራቢያቸውና ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው መንትያዎች በአንድ ቦታ እንዲመደቡ እንዲሁም ፥ የጤና ችግር ያለባቸው ባቀረቡት ማስረጃ መሰረት ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል ።
በዘንድሮው ድልደላ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሴቶች ቁጥር ተመጣጣኝ እንዲሆን ተደርጓል ።
በኮምፒውተር ታግዞ የተከናወነው ምደባ የተማሪዎችን ውጤት ፣ የትምህርት መስክንና የዩኒቨርሲቲ ምርጫን መሰረት በማድረግ በውድድር ብቻ ተከናውኗል ብሏል ኤጀንሲው ።
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 7 ሺህ 312 ተማሪዎቸን በመቀበል ቀዳሚው ሲሆን ፥ አዳማ ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 134 ተማሪዎች በመቀበል በሁለተኝነት ሲቀመጥ ፥ 4 ሺህ 495 ተማሪዎችን የተቀበለው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ነው ።
ዝቅተኛ ቁጥር ያለው ተማሪ የተቀበለው ኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ 955 ተማሪዎች ተመድበውለታል ።
http://www.fanabc.com

No comments:
Post a Comment