ቀትር 8 ሰአት ላይ ደግሞ በሴቶች ማራቶን ፥ ቲኪ ገላና ፣ አበሩ ከበደ ፣ ፈይሴ ታደሰ ፣ መሰረት ሃይሉና መሰለች መልካሙ በሞስኮው ጎዳናዎች ኢትዮጵያን ወክለው 42 ኪሎ ሜትሩን ይሮጣሉ።
ማምሻውን 11 ሰአት ከ20 ላይ ደግሞ ፤ ሶፊያ አሰፋ ፣ ህይዎት አያሌው ፣ እቴነሽ ዲሮ በ3 ሺህ መሰናክል ሴቶች ይወዳደራሉ።
ኢትዮጵያውያን የበላይ የሆኑበት እና ለወርቅ ሜዳልያ የሚጠበቁበት የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜም ፥ 12 ሰአት ከ55 ሲካሄድ ፤ ደጀን ገብረመስቀል ፣ አበራ ኩማ ፣ ኢማነ መርጊያና ኢብራሂም ጀላን የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ ይሮጣሉ።
No comments:
Post a Comment