Pages

Thursday, September 1, 2011

3 ሴት ተጨዋቾች ደቡብ አፍሪካ ኮበለሉ

the LUCY
(ሊብሮ) ደቡብ አፍሪካ የሄደው የሴቶች ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ጎል ሳያገባ መጣ፡፡ ቀደም ሲል 2ለ1 አሸንፎ ነበር፡፡ በአሁኑ 3ለ0 ተሸነፈ፡፡ እንቅስቃሴያቸው ደህና ነበር፡፡ ግን እየተበጣጠሱ አጥቂዎቹ በግል ስለሚገኙ ለነኛ ተመችቷቸው ተሸናፊ ሆነዋል፡፡ አሁን ላወራላችሁ የፈለግኩት ደቡብ አፍሪካ የሴት ተጨዋቾች መኮብለያ መሆኗን ነው፡፡ ወንድ ተጨዋቾች በተለያዩ አገራት ኮብልለዋል ቁጥራቸውም በጣም ብዙ ነው፡፡ ሴቶች ግን እሲካሁነ 3 ብቻ ናቸው የኮበለሉት፡፡ 3ቱም ደቡብ አፍሪካ ነው የጠፉት፡፡ ከወንድ ተጨዋቾ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮበለለው ሙሉጌታ የተ ባለ የጊዮርጊስ በረኛ ነው፡፡ ጊዜውም በ1946 ሲሆን ቦታውም ሲውዲን ነው፡፡ ከሴት የእግር ኳስ ተጨዋች ለመጀመሪያ ጊዜ የኮበለለችው ሙና ትባላለች፡፡ ቦታውም ደቡብ አፍሪካ ሲሆን ጊዜውም በ 1997 ነው፡፡ ሙና ደቡብ አፍሪካ የሰፈሯን ልጅ አገኘች 2 ቀን አብረው አወሩ በ3ተኛው ቀን ይዘዋት ሄዱ ከዚያ በኋላ 2ተኛው ኩብለላ የታየው እዚው ደቡብ አፍሪካ ነው፡፡ ዘይቱናና ኤደን ናቸው የጠፉት፡፡ ሻይ አብረው ነው የጠጡት የተወሰነ ጊዜ አብረው አውርተዋል፡፡ ከጨዋታ በኋላ እራት ኤምባሲው ጋብዟቸው ሄዱ ከዚያ ሲመለሱ ዘይቱና ከቡድኑ ጋር ተለየች ከዚያ ቁጥጥር ተደረገ፡፡ ጠዋት ወደ ኤርፕርት ሲሄዱ ሰርቪስ ውስጥ ሲገቡ ኤደን የት እንደገባች አልታወቀም በኋላ መኮብለሏ ታወቀ፡፡ ደቡብ አፍሪካ የሴቶች አስኮብላይ አገር ሆናለች፡
http://www.zehabesha.com/

No comments:

Post a Comment