• አምስት የግብፅ ጳጳሳትም ድምፅ ይሰጣሉ
• በዓለ ሲመቱ በኮፕቲክ ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛውን ፓትርያርኳን ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ውስጥ እንደምትመርጥ አስታወቀች፡፡
ለፓትርያርክነት የሚወዳደሩት አምስቱን ዕጩዎቿንም ባለፈው ሰኞ ይፋ አድርጋለች፡፡ • በዓለ ሲመቱ በኮፕቲክ ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛውን ፓትርያርኳን ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ውስጥ እንደምትመርጥ አስታወቀች፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የካቲት 18 ቀን በመንበረ ፓትርያርክ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ለፓትርያርክነት የሚወዳደሩት አምስቱ ዕጩዎች ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ (ዕድሜ 71)፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ዕድሜ 75)፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ዕድሜ 61)፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ፣ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ዕድሜ 59)፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ዕድሜ 50) ናቸው፡፡